Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ፀረ-ሚሳኤል ወደ ዩክሬን ከላከች ሩሲያ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ፓትሪዮት የተሰኘውን ዘመናዊ ፀረ-ሚሳኤል ወደ ዩክሬን የምትልክ ከሆነ አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች፡፡

አሜሪካ ፓትሪዮት የተሰኘውን እጅግ ዘመናዊ የሚሳኤል መቃወሚያ ወደ ዩክሬን ለመላክ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቋን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚሳኤሉን በዩክሬን ምድር ለሚፈለገው አላማ ለማሰማራትም የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፊርማ ብቻ እንደቀረው ተመላክቷል፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ዋሺንግተን ፀረ-ሚሳኤሉን ወደ ዩክሬን ለመላክ ማቀዷ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነታ በቀጥታ ተሳታፊ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

ወደ ዩክሬን የሚላኩ የአሜሪካ ዘመናዊ ጦር መሳሪያዎች የሩሲያን ሃይሎች ኢላማ የሚያደርጉ ናቸው ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

የአሜሪካ እቅድ ግልጽ የጠብ አጫሪነት ድርጊት መሆኑን ጠቁመው እቅዱ እውን የሚደረግ ከሆነም ሩሲያ አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ ትወስዳለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.