Fana: At a Speed of Life!

በህጻናት ልብ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና ፕሮግራም ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስቴር እና በኮንጂኒታል ኸርት አካዳሚ መካከል በህጻናት ልብ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና ፕሮግራም ላይ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ በዋናነት የአካዳሚክ ድጋፍ እና የስፔሻሊቲ ህጻናት ልብ ህክምና የሚሰጡ ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም የህጻናት ልብ ሕክምና አገልግሎትን ለማሻሻል እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ስምምነቱ ሁሉን አቀፍ እና ቀጣይነት ያለው የልብ ህክምና መርሐ ግብርን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሙያዊ እድገትን በልምድና በስልጠና በማሻሻል የልብ ህክምና ፕሮግራም ስኬታማ እንዲሆን እና በኢትዮጵያ የልብ ህመምተኞች የህክምና አገልግሎት ፍላጎቶችን ለማሟላት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮንጄኔታል ኸርት አካዳሚ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አጋቲ ሳልቫቶሬ በበኩላቸው÷ ትብብሩ በህጻናት የልብ ህክምና አቅም ለማሳደግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር መናገራቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.