Fana: At a Speed of Life!

የደጎዲያ ጎሳ ባህላዊ መሪ ወባር አብዲሌ ወባር አብዲ የሰላም የክብር ሚዳሊያ ርክክብ በጅግጅጋ እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደጎዲያ ጎሳ ባህላዊ መሪ ወባር አብዲሌ ወባር አብዲ የሰላም የክብር ሚዳሊያ ርክክብ ሥነ-ሥርአት በጅግጅጋ ቤተ መንግሥት እየተካሄደ ነው።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ ከጎረቤት ኬንያና ሶማሊያ የመጡ የአስተዳደርና ባህላዊ ማህበረሰብ መሪዎች፣ የፌዴራል አካላት፣ አባገዳዎች፣ የሶማሌ ክልል ሀገር ሽማግሌዎች ሸንጎ አባላት፣ ኡለማዎች፣ ሴቶችና ወጣቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያ ፣ በሶማሊያና በኬንያ የሚገኘው የዲጎዲያ ጎሳ ባህላዊ መሪ ወበር አብዱላሂ ወበር አብዲ በግጭቶች ምክንያት በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከተለያዩ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጋር በጋራ የሚሰሩ የሰላም አባት መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።

የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ከሶማሌ ማህበረሰብ ጎሳዎች መካከል አንዱ በሆነው ደጎዲ ጎሳ ባህላዊ መሪ ወባር አብዲሌ ወባር አብዲ በቀጠናው ሰላም ለማስፈን ያበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ለማስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተመላክቷል።

በኬንያው ልዑክ ከቀድሞው የኬኒያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ የተበረከተውን የሰላም ሜዳሊያ ሽልማት ለወባሩ ያበረክታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

በተለይ ወባር አብዲሌ መልካም ስራዎችን ከፍ ለማድረግ ለሰላም ያላቸው አርዓያነት ሌሎች እንዲተላለፍ ለማበረታታት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኦሁሩ ኬንያታ ያበረከቱትን የክብር የሰላም ሚዳሊያ ይፋዊ በሆነ መንገድ ይረከባሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ወበር አብዱላሂ ወበር አብዲ በሶማሌ ክልል ከህዝቡ ተቀባይነትን ያተረፉና ከፍተኛ ክብር ከሚሰጣቸው ባህላዊ የጎሳ መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.