Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ውስጥ ገቢ ለማሳደግና ለልማት የሚውሉ ወጪዎችን ለመሸፈን የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል – ገንዘብ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ ገቢ ለማሳደግና ለልማት የሚውሉ ወጪዎችን ለመሸፈን የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ተናገሩ፡፡

የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ፣ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም የገቢዎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ከክልል የገንዘብ፣ የፕላንና የገቢ ቢሮዎች ጋር የምክክር ጉባዔ በአርባምንጭ ምንጭ ከተማ እያካሄዱ ይገኛል።

አቶ አህመድ ሺዴ ÷ የክልል የገንዘብ፣ የፕላንና የገቢ ቢሮዎች ባለድርሻ አካላት በየጊዜው በመገናኘት የሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ በመመካከር ቀጣይነት ያለው ለውጥ እንዲመዘገብ እንዲሰሩም ጠይቀዋል።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት የገጠሙ ፈተናዎች የገቢና ልማት ዘርፉን የጎዱ ቢሆንም ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ለማስቀጠል ያሉ ዕድሎችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ከፍተኛ ሥራ መሥራት አለብን ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.