Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ባንክ የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቁመና ላይ እገኛለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲዳማ ባንክ አክሲዮን ማህበር የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስታወቀ፡፡

ባንኩ የባለ አክሲዮኖች 24ኛ መደበኛ 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በሐዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ÷ ባለፉት ጊዚያቶች የተከናወኑ ስራዎችን ከማንሳት ባለፈ በቀጣይ ባንኩ ስለሚሰራቸው ተግባራትም ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኩ ነባር የማይክሮ ፋይናንስ ስራዎችን ከማጠናከር ጎን ለጎን ከብሔራዊ ባንክ የስራ ፍቃድ ለማግኘት ፣ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችንና ሌሎች ተግባራትን እንዳከናወነ ቦርዱ ገልጿል።

ባንኩ የውስጥ አሰራር ስራዎችን የሚመራበትን ፖሊሲዎች፣ ደንቦችን መመሪያዎችንና የአሰራር ማኑዋሎችን ማዘጋጀትና የማፀደቅ ተግባራትን ማከናወኑም ነው የተጠቀሰው፡፡

የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ አስር ቅርንጫፎችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማዘጋጀትና ውስጣዊ አደረጃጀቶችን ማሟላትና መሰል ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

በብርሃኑ በጋሻውና ደብሪቱ በዛብህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.