Fana: At a Speed of Life!

ተንቀሳቃሽ ንብረትን በዋስትና በማስያዝ ከባንኮች ብድር ማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተንቀሳቃሽ ንብረትን በዋስትና በማስያዝ ከባንኮች ብድር ማግኘት የሚያስችል ስርዓት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

ተንቀሳቃሽ ንብረትን ዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለው አዋጅ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ገልፀዋል።

አዋጁ በተለይም ገጠራማውን የአገሪቱ አከባቢ ተጠቃሚ ያደርጋል ያሉ ሲሆን÷በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች እስከአሁን ከ330ሺህ ለማይበልጡ ስዎች ብቻ ብድር መስጠታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በአገሪቷ ካሉት ዜጎች አንጻር ብድር የወሰዱ ዜጎች እጅግ አነስተኛ መሆናቸውንም አንስተው አሁን ላይ ይህን ችግር ለመፍታት ተንቀሳቃሽ ንብረትን በዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት የሚሰጥበት አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በዚህም በተለይ አርብቶ አደሩ እና አርሶ አደሩ እንስሳትን፣ ግመሎችን ፣ የግል ደኖችን፣ የመሬት መጠቀሚያ ደብተሮችን እና የመሬት መብትን በማስያዝ እና በሌሎችም ብድር ማግኘት የሚያችል መሆኑን አመላክተዋል።

ይህ አዋጅም በቅርቡ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ይፋ እንደሚደረግም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.