Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በአርጀንቲና እና በፈረንሳይ መካከል ዛሬ ይካሄዳል፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ህዳር 20 በኳታር መካሄድ የጀመረው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡

በዓለም ዋንጫው 32 ሀገራት ተሳትፈዋል፤ሴኔጋል ፣ጋና፣ ካሜሮን፣ ቱኒዚያና ሞሮኮ ደግሞ አፍሪካን የወከሉ ሀገራት ሲሆኑ÷ ሞሮኮ እስከ ግማሽ ፍፃሜው በመጓዝ ብርቱ ተፋላሚም መሆን ችላለች፡፡

ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ብትችልም በፈረንሳይ 2 ለ 0 ተሸንፋ ለፍጻሜው ሳታልፍ ቀርታለች፡፡

በዚህም ሞሮኮ ትናንት በተካሄደ የደረጃ ጨዋታ በክሮሺያ 2 ለ 1 ተሸንፋ አራተኛ ደረጃን በመያዝ የአለም ዋንጫውን አጠናቃለች፡፡

አርጀንቲና እና ፈረንሳይ ለፍፃሜው የደረሱ ሀገራት ሲሆኑ÷ ምሽት 12 ሰዓት ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርጉት ብርቱ ፉክክር በጉጉት ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.