Fana: At a Speed of Life!

የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የለውጡ መንግስት በቁርጠኝነት ይሰራል – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የለውጡ መንግስት በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስራ አመራር ተቋም ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባው ዘመናዊ አዳራሽ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ተመርቋል፡፡
 
አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡
 
ፕሮጀክቶቹ የሲሚንቶ እና የነደጅ አቅረቦት እጥረት ቢያጋጥማቸውም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩ ለመፍታት ይሰራል ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የስራ አመራር ተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ የኋንስ ተሰማ በበኩላቸው÷ የተቋማት ግንባታ ለማዘመንና ለማጠናቀቅ መንግስት ባስቀመጠው ዕቅድ መሰረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.