Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቡና አውደ ርዕይ በለንደን ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ኢትዮ- ቡና አስመጪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጋራ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ቡና አውደ ርዕይ ዛሬ በለንደን ተከፍቷል።

ኤግዚቢሽኑ የእንግሊዝ እና ዓለም አቀፍ ቡና ገዢዎችን ከኢትዮጵያ አረንጓዴ እና የተቆላ ቡና አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ መሆኑ ተገልጿል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ በኢትዮጵያ እና እንግሊዝ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ለማበረታታት እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ ይህ ጥረትም ኢትዮጵያ የቡና መገኛ በመሆኗ የሚበረታታ ነው ተብሏል።

ጠንካራ የግብይት ሥርዓት በመዘርጋት በእንግሊዝ ያለውን የቡና ገበያ ድርሻ ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡፡

የዓለም አቀፉ የቡና ድርጅት ዋና ኢኮኖሚስት ዶ/ር ዴኒስ ስዩዲ÷ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ መሆኗን በማንሳት÷ ኢትዮጵያ የአይኮ አባል እና ቡናን ከሚልኩ ዋና ዋና ሀገራት አንዷ ነች ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተወካይ እና የቲፒካ ቡና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሚኒሊክ ሃብቱ በበኩላቸው÷ ዝግጅቱ በልዩ ጣዕም የሚታወቀውን ኢትዮጵያ ቡና ለማስተዋወቅ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.