Fana: At a Speed of Life!

አርጀንቲና የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲና ፈረንሳይን በመለያ ምት በማሸነፍ የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
 
የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሉሳይል አይኮኒክ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
 
በዚህም ፈረንሳይ እና አርጀንቲና መደበኛ ጨዋታውን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን÷ ተጨማሪ 30 ደቂቃውንም 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡
 
የፍጻሜ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም አርጀንቲና ፈረንሳይን በማሸነፍ ከ36 ዓመታት በኋላ የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችላለች፡፡
 
ድራማዊ ትዕይንት ባስተናገደው የፍጻሜ ጨዋታ ኬሊያን ምባፔ ከ92 ዓመታት በኋላ በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡
 
ድራማዊ ትዕንት ባስተናገደው የፍጻሜ ጨዋታ ኬሊያን ምባፔ ከ92 ዓመታት በኋላ በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡
 
ምባፔ በ22ኛው የኳታሩ የዓለም ዋንጫም ስምንት ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢ መሆን ችሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.