Fana: At a Speed of Life!

የፕሪሚየር ሊጉ የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።

በዓለም ዋንጫው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት እንደሚጀመርም ተገልጿል።

ባህር ዳር ከተማ ከመቻል ከቀኑ 10 ሰአት እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና ከምሽቱ 1 ሰአት በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ነገ ፋሲል ከነማ ከወልቂጤ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰአት ኢትዮጵያ ቡና ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ይጫወታሉ።

የፕሪሚየር ሊጉ 13ኛ ሳምንት መርሐግብር እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.