Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ “የብሉ ኢኮኖሚ” ልማት ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ “የብሉ ኢኮኖሚ” ልማት ስትራቴጂ ይፋ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የብሉ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ የውቅያኖስ፣ የሐይቅና የባህር ሃብቶችን እንዲሁም ወደቦችን በዘላቂነት ጥቅም ላይ ማዋልን ማዕከል ያደረገ የልማት ዘርፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ጋር በመተባበር እንዳዘጋጀው ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ሚኒስትሯ የአምራች ዘርፉን ትርፋማነትና ተወዳዳሪነት ለመጨመር ፕሮጀክቱ በቀጣይ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.