Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዙሪያ ያሉ የፈረንሳይ ደጋፊዎችን በማስደሰታችሁ ኮርተንባችኋል – ኢማኑኤል ማክሩን ለብሄራዊ ቡድናቸው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በዓለም ዙሪያ ያሉ የፈረንሳይ ደጋፊዎችን በማስደሰታችሁ ኮርተንባችኋል ሲሉ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በፍፃሜ ጨዋታው በአርጅንቲና በመለያ ምት ተሸንፎ ዋንጫውን ያጣውን ብሄራዊ ቡድናቸውን መልበሻ ክፍል ድረስ በመሄድ አፅናንተዋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ ምስሎች እንደሚያሳዩት በጨዋታው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ጎል በማስቆጠር ፈረንሳይን ወደ ውድድሩ የመለሰው ኬሊያን ምባፔን ፕሬዚዳንቱ አቅፈው ሲያፅናኑት ተስተውለዋል፡፡

ማክሮን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በትዊትር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክትም አርጀንቲና ላስመዘገበችው ድል እንኳን ደስ ያለችሁ ያሉ ሲሆን፥ የፈረንሳይ ተጫዋቾችን እጅ አልሰጥም ባይነት አወደሰዋል፡፡

ለቡድኑ ባስተላለፉት መልዕክትም በአለም ዙሪያ ያሉ የፈረንሳይ ደጋፊዎችን አስደስታችኋል፤ በእናንተም ኮርተናል ብለዋል፡፡

ፈረንሳይ በ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ክሮሺያን 4 ለ 2 በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆኗን አልጀዚራ አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.