Fana: At a Speed of Life!

ተመድ የታዳጊ ሀገራትን የብዝኀ ሕይወት ጥበቃ ለመደገፍ የ20 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ ረቂቅ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) ተመድ ለብዝኀ-ሕይወት ጥበቃ ይውል ዘንድ ለታዳጊ ሀገራት የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ በዓመት ቢያንስ ወደ 20 ቢሊየን ዶላር እንዲያድግ የሚጠይቅ ረቂቅ አቀረበ፡፡

ተመድ ያቀረበው ረቂቅ በኢኮኖሚ የበለጸጉ ሀገራት ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ የሚተገብሩት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ዓለም አቀፉን የገንዘብ ድጋፉ በፈረንጆቹ 2030 ቢያንስ ወደ 30 ቢሊየን ዶላር ማሳደግ እንደሚገባም መጠየቁን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

ድጋፉ ታዳጊ እና ትናንሽ ደሴታማ ሀገራትን እንደሚያካትት ተጠቁሟል፡፡

15ኛው በብዝኀ ሕይወት ላይ የመከረውን የተመድ ኮንቬንሽን ጉባዔ በካናዳ ሞንትሪያል ተካሂዷል።

የዘንድሮውን ጉባዔ ቻይና የመራችው ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ 2030 በፍጥነት የሚተገበሩ 23 ያህል የድርጊት መርሐ-ግብሮች ተካተውበታል፡፡

ጉባዔው በ2030 ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆኑትን የተራቆቱ መሬቶች፣ ምንጮች ፣ የባሕር ዳርቻዎች እና የባሕር ብዝኀ-ሕይወት ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ ዓላማ ሰንቋል፡፡

ጉባዔው ከፈረንጆቹ ታኅሣሥ 7 እስከ 19 ቀን ድረስ ነው የተካሄደው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.