Fana: At a Speed of Life!

ለውጭ ገበያ ከቀረበ የሥጋ ምርት ከ41 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) ባለፉት አምስት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ የሥጋ ምርት 41 ሚሊየን 800 ሺህ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ገለጸ።
በባለሥልጣኑ የኤክስፖርት ቄራ ኢንስፔክሽንና ሰርተፊኬሽን ዳይሬክተር አያሌው ሹመት ÷ ገቢው 5 ሺህ 900 ቶን የሥጋ ምርት በማቅረብ እንደተገኘ ተናግረዋል፡፡
የሥጋ ምርቱ በስፋት ከተላከባቸው አገራት መካከል ዱባይ፣ ሳዑዲ አረቢያና ኩዌት እንደሚገኙበት ነው የገለጹት።
በቻይና፣ ኢንዶኔዥያ፣ እንዲሁም በአውሮፓ አገራት በቀጣይ የሥጋ ምርት ለመላክ የሚያስችሉ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።
አሁን ባለ አቅም በየዓመቱ 200 ሺህ ቶን የሥጋ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚቻል ጠቁመው÷ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.