Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአርሶ አደሮች የዲጂታል ግብይትን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርሶ አደሮች ዲጂታል የግብይት ስርዓትን ተጠቅመው የግብርና ምርቶችን የሚገበያዩበት አሰራር ይፋ አድርጓል።

ንግድ ባንክ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ጋር ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ አርሶ አደሮች ከኤጀንሲው የሚገዟቸውን ማዳበሪያና የግብርና ቁሳቁስ የሞባይል ክፍያን በመፈጸም ወደ ባንክ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ምርቶቻቸውን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በየቀበሌውከሚገኙ የግብርና ምርት አቅራቢ ማህበራትም አርሶአደሮች የጥሬ ገንዘብ ክፍያ መክፈል ሳይጠበቅባቸው የሞባይል ባንክን ወይም ሲ ቢ ኢ ብርን በመጠቀም ማደበሪያን ጨምሮ የግብርና ምርቶች ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

ቀድመው በሲ ቢ ኢ ብር ኤጀንሲዎች አማካኝነት የባንክ ደብተር መክፈት ሳይጠበቅባቸው እስከ 30 ሺህ ብር በማጠራቀም የግብርና ግብዓቶችን መግዛት እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ስምምነቱ የግብርና እንቅስቃሴውን እንደሚያቀላጥፍ ጠቅሰው፥ በተለይም በዘር ወቅት አርሶ አደሩ ሩቅ ቦታ ሄዶ የባንክ ወረፋ በመጠበቅ የሚያጠፋውን ጊዜ ይቀንሳል ብለዋል፡፡

በቀጣዩ አመትም ግብይቱን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝድ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል።

በትግስት ብርሃኔ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.