Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለ3 ክልሎች 45 ሚሊየን ብር የሚገመት የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና ለቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ይሆን ዘንድ ለ3 ክልሎች የ45 ሚሊየን ብር የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉ ለአማራ፣ ለኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የሚሰጥ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶቹ ከነገ ጀምሮ ለየክልሎቹ የማከፋፈል ስራ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ ተናግረዋል።

የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፉ  በቀጣይ ለሌሎች ክልሎች እንደሚካሄድ ኃላፊዋ  መግለጻቸውን ኢ.ዜ.አ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.