Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ የተመራ ልዑክ የ3ኛውን አየር ምድብ የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ የተመራ ልዑክ የሶስተኛውን አየር ምድብ የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል፡፡
 
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ተሳትፈዋል፡፡
 
ከፍተኛ አመራሮቹ የኢትዮጵያን አየር ኃይል በ2022 ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል አንዱ ለማድረግ የተጀመረውን የከፍታ ጉዞ ከግብ ለማድረስ ሶስተኛው አየር ምድብ የሚያከናውነውን የሥራ ላይ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
 
የምድቡ ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ደረጄ ቡሽሬ÷ምድቡ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት ከመወጣት ባለፈ በስሩ የሚገኘው የበረራ ትምሀርት ቤት በአዳዲስ ተክኖሎጂ በመታገዝ ብቃት ያላቸው አብራሪዎችን እያበቃ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
 
በአየር ምድቡ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ለማሥቀጠል እና ምቹ የስራ ቦታን የመፍጠር ጅምሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማብራራታቸውንም የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.