Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ሲሰጥ የነበረውን የባንክ አገልግሎት ለማቋረጥ መገደዱን ባንኩ አስታውሷል።

በቅርቡ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፥ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል አንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.