Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ በቀን ከ150 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎችን እያስተናገደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ቀጣና ለማሳለጥ የተገነባው ዘመናዊ ደረቅ ወደብ ከጅምሩ በቀን ከ150 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎችን እያስተናገደ መሆኑን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ነፃ የንግድ ቀጣና አቅራቢና ደንበኞቹን በቅርበት ማግኘት የሚችልበት መድረክ ነው፡፡

በቀጣናው ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል አንዱ ሎጂስቲክስ በመሆኑ ዓላማውን ሊያሳካ የሚችል ዘመናዊ ደረቅ ወደብ መገንባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በቀጣናው ውስጥ ነፃ የንግድ አገልግሎት የሚሰጥ የሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በቅርበት አገልግሎት ለማግኘት ከማስቻሉም ባለፈ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘትና የስራ ዕድል በመፍጠር የጉላ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው እና በጥራቱ በአፍሪካ ምርጥ የሚባለው የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ቀጣናው የተቋቋመለትን ዓላማ ለማሳካት ያግዛልም ነው የተባለው።

በዚህም ወደቡ ገና ከጅምሩ በቀን እስከ 150 ተሽከርካሪዎችን በማስተናገድ የተሳለጠ የሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.