Fana: At a Speed of Life!

በኅገ ወጥነት ሲዘዋወር የነበረ 4 ኪሎ ግራም “ማግናታይት” የተባለ ማዕድን ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥነት ሲዘዋወር የነበረ አራት ኪሎ ግራም የሚመዝን ማግናታይት የተባለ ማዕድን በሀረር ከተማ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በደረሰው መረጃ እና በተደረገ የክትትል በሀረር ከተማ ማእድኑን ሲያዘዋውሩ የተገኙ

ሦስት ተጠርጣዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ስራ ላይ ተሳትፎ ላደረጉ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የኢንተለጀንስ ባለሙዎች እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.