Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱን ትውልድ በቴክኖሎጂው መስክ ማሰልጠን ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ትልቅ ሚና አለው – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ወጣት በሆነበት ሀገር ወጣቱን ትውልድ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ማሰልጠን እና ማብቃት ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ትልቅ ሚና አለው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከ “አይ ኮግ ኤ ሲ ሲ” መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ቤተልሄም ደሴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ድርጅቱ ታዳጊ ልጆች በተለይም ሴት ልጆች ላይ የሚያተኩሩ የቴክኖሎጂ ትምህርት ስራዎች እንዲሁም በቅርቡ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር ስላስመረቁት ዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ፕሮጀክት ዙሪያ መክረዋል፡፡

የ”አይ ኮግ ኤ ሲ ሲ” ፕሮጀክት የሆነው ዲጂትራክ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች እኩል የሆነ እድል ተሰጥቷቸው የኮድዲንግ፣ የሮቦቲክስ እና ሌሎች አዳዲስ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ መስራት ዋነኛው ትኩረቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በታለሙ አካባቢዎች ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የማገናዘብ፣ የችግር ፈችነት እና የፈጠራ ክህሎት የማዳበር ትምህርት ያለውን ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጥ መሆኑም ተመላክቷል።

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የ“አይ ኮግ ኤ ሲ ሲ” እና ዲጂትራክ ኢትዮጵያን ስኬት ለማየት ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.