Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊየን በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ  እንዳመላከተው÷ ወረርሽኙ በሀገሪቱ በተከሰተባቸው ሶስት ዓመታት ውስጥ 100 ሚሊየን 2 ሺህ 248 ዜጎች በቫይረሱ ሲያዙ 1 ሚሊየን 88 ሺህ  በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

የካሊፎርኒያ ግዛት11 ነጥብ 6 ሚሊየን የቫይረሱ ታማሚዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚ ስትሆን÷ ቴክሳስ 8 ነጥብ 1 ሚሊየን እንዲሁም ፍሎሪዳ 7 ነጥብ 3 ሚሊየን የቫይረሱ ታማሚዎችን ያስመዘገቡ ግዛቶች ናቸው፡፡

በሀገሪቱ በተያዘው ወር ከተመዘገቡ የኮቪድ- 19 ታማሚዎች መካከል 70 በመቶ ሚሆኑት ኦሚክሮን ቫሪየንት በተሰኘው የኮቪድ-19 ዝርያ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ የተጠቃች ሀገር ስትሆን÷ በዓለም በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ከሚዳረጉ ሰዎች ውስጥ 16 በመቶውን እንደምትሸፍን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.