Fana: At a Speed of Life!

የቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች ገበያው የሚፈልገውን ተወዳዳሪ የሰው ሀይል በማፍራት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

የሐረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ባገኘው ከ28 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ የተከናወነ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ሰርቶ ማሳያና የዳታ ማዕከል ተመርቋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ እንዳሉት ፥ ያለውን የሰው ኃይል በአመለካከት፣ በክህሎትና በእውቀት በማነጽ በአግባቡ መጠቀም ይገባል።

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ማዕከሉ ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ከመስጠት አንፃር ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገበያው የሚፈልገው ዓይነት የስራ ዘርፍ መርጦ ማሰልጠንና ተወዳዳሪ የሆነ ወጣት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሐረሪ ክልል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሚልኬሳ አህመድ በበኩላቸው ፥ ማዕከሉ የቴክኖሎጂ ሽግግር አቅምን ለማሳደግ፣ ወጪ ለመቆጠብ፣ የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና የመማር ማስተማር ሂደትን ለማቀላጠፍ ያግዛል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.