Fana: At a Speed of Life!

የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላት በገንዘብ እና በጉልበት ኅብረተሰቡን እየደገፉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላት በገንዘብ እና በጉልበት ኅብረተሰቡን እየደገፉ እንደሚገኝ የዕዙ የሚዲያ እና ሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ።

የዕዙ ሠራዊት አባላት በ2015 ኅዳር ወር ብቻ 41 ሔክታር ማሳ ላይ የሚገኝ የአቅመ ደካማ አርሶአደሮችን ሰብል መሰብሰብ መቻላቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አባላቱ ከ600 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ከደመወዛቸው በማዋጣት ለተቸገሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጋቸውም ነው የተመላከተው፡፡

ከሕክምና ድጋፍ ጋር በተያያዘም ለ73 ሰዎች የጤና ምርመራ እና የመድሐኒት ድጋፍ ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡

በዕዙ ስር በሚገኙ የህክምና ክፍሎችም ለ21 ሰዎች የአንቡላንስ አገልግሎት መሥጠት መቻሉ ተጠቁሟል።

ነፍሰ-ጡሮች በክፍለ ጦሩ የጤና ሙያተኞች ወሊድን ጨምሮ ሌሎች የሕክምና አገልግሎት ማግኘትም እየቻሉ ነው ተብሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግዳጅ በሚወጣባቸው አካባቢዎች ሁሉ አቅም በፈቀደ መልኩ ካለው ላይ እያካፈለ፣ የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ለኅብረተሰቡ በቦቲ ውሃ እያቀረበ እንዲሁም ሰብል በማጨድ እና በመሠብሠብ ሕዝባዊነቱን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.