Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንግስት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 6 የጂቡቲ ወታደሮችን አስለቅቋል- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ፍሩድ በሚባሉ ታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት የጂቡቲ ወታደሮችን በሰላማዊ መንገድ ማስፈታት መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክቶሬት ጄነራል አምባሳደር ፍሰሐ ሻውል በሰጡት መግለጫ÷ መንግስት ከአፋር ክልል ጋር በመተባበር ፍሩድ የሚባል ታጣቂ ያገታቸውን ስድስት የጂቡቲ ወታደሮች አስለቅቋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ስድስት ወታደሮችን በሰላማዊ መንገድ ማስፈታት እንደቻለ የገለጹት አምባሳደር ፍሰሐ÷ ኢትዮጵያና ጂቡቲ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከጅቡቲ መንግሥት በቀረበለት ይፋዊ ጥያቄ መሠረት ወታደሮቹን ለማስለቀቅ ከጥቅምት ወር መጨረሻ አንሥቶ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡

ወታደሮቹ ለጂቡቲ መንግስት መተላለፋቸውንም ነው የተናገሩት።

በአሸናፊ ሽብሩና ምስክር ተስፋዬ

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.