Fana: At a Speed of Life!

ሃሰተኛ ብርና ዶላር ሲያዘዋውሩ ተገኝተዋል የተባሉ ግለሰቦች ተከሰሱ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 100 ሺህ ሃሰተኛ ብር እና የአሜሪካ ዶላር ሲያዘዋውሩ ተገኝተው በቁጥጥር ስር ውለዋል በተባሉ አምስት ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በመዲናዋ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አፍንጮ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው የተመላከተው፡፡

በወቅቱ 100 ሺህ ሃሰተኛ ብርና 7 ሺህ 100 የአሜሪካ ዶላር በእጃቸው ላይ እንደተገኘና በቁጥጥር ስር በዋሉት አምስት ተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊው ምርመራ ከተጣራ በኋላ በአቃቤ ህግ ክስ እንደተመሰረተባቸው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሃሰተኛ የገንዘብ ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥና በግብይት ወቅትም ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.