Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አምባሳደሮች የመከላከያ ሚኒስቴርን እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች የመከላከያ ሚኒስቴርን እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን ጎበኙ፡፡

አምባሳደሮቹ በመከላከያ ሚኒስቴር በነበራቸው ጉብኝት ሚኒስቴሩ ባካሄደው ሪፎርም በቅርብ ጊዜ ያልነበሩ አደረጃጀቶችን መስርቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ ተገልፆላቸዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ መኳንንቴ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት ÷ ባሕር ኃይል እና ሳይበርን ጨምሮ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን የሚያስከብሩ የደኅንነት መዋቅሮች ተመስርተዋል፡፡

እንዲሁም አምባሳደሮቹ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን ጎብኝተዋል፡፡

የአስተዳደሩ ም/ዋና ዳይሬክተር ዳንዔል ጉታ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት ÷ የሳይበር ዲፕሎማሲ አራተኛው ምኅዳር እንደመሆኑ መጠን የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የዲፕሎማቶች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የአስተዳደሩ ም/ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው÷ በሳይበር ዲፕሎማሲ ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ማዕቀፎች (ፍሬም ወርኮች) ላይ ለመነጋገር የአምባሳደሮቹ ጉብኝት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡

በሳይበር ዲፕሎማሲ፣ በሳይበር ተሰጥዖ ልማት እናበሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ ላይ ኢመደአ ለሚያደርገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚያበረክቱ ጎብኝዎቹ መናገራቸውን የየተቋማቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.