Fana: At a Speed of Life!

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የኩፍኝ መከላከያ ክትባት በይፋ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

የማስጀመሪያው ሥነሥርአት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሰርጥ ጤና ጣቢያ ነው የተካሄደው።

የማስጀመሪያ ሥነሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እና ሌሎች የጤና ሚኒስቴር እና የክፍለከተማው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት መካሄዱ ተገልጿል፡፡

በክትባቱ ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት ሊከተቡ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል፡፡

ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 22 ቀን ይሰጣል ነው የተባለው፡፡

ክትባቱ በስድስት የመንግስት ሆስፒታሎች በ101 የመንግስት ጤና ጣቢያዎች ከሰኞ አስከ አርብ በስራ ስአት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 9 ወር እስከ 5 ዓመት የሆናቸው ከ15 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕጻናት የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባቱን ያገኛሉ ተብሏል።

በተያያዘም በአዲስ አበባ ከተማ ከ5 ዓመት በታች ለሆናቸው ለ520 ሺህ ህጻናት ክትባቱ እንደሚሰጥም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በቅድስት ብርሃኑ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.