Fana: At a Speed of Life!

ዕደጋ በርኸ፣ ሰመማና ማይ ሓንስ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕደጋ በርኸ፣ ሰመማና ማይ ሓንስ ከተሞች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝተዋል፡፡

ለረጅም ጊዜ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የቆዩትና ከአክሱም ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ የሚያገኙት የዕደጋ በርኸ፣ ሰመማ ከተሞች ዛሬ አገልግሎቱን አግኝተዋል፡፡

ከሽረ ማከፋፈያ አገልግሎት የሚያገኙት ዛናና ማይ ሓንስ ከተሞችም አገልግሎት እንዳገኙ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓዲ ዳሮ ከተማና በአካባቢው በሚገኙ ሌሎች ከተሞች ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ተቋሙ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በተከሰተው ጦርነት በኤሌክትሪክ ማሰራጫ መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ከስር ከስር መልሶ በመጠገን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች ዳግም ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.