Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የበጎ ፈቃድ ባለሙያዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የበጎ ፈቃድ ባለሙያዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ።

በመንግሥትና በበጎ ፈቃደኛ ሰዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ወደፊት የወረርሽኙ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ በርካታ የበጎ ፈቃድ ባለሙያዎችን ማሰማራት ስለሚጠይቅ በጎ ፈቃደኞች እንዲመዘገቡ ጥሪ ማቅረቡ ነው የተነገረው።

በዚህ መሰረት

1. በጤና ሙያ ተመርቀው ወደ ሥራ ያልተሰማሩ

2. መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት እየሰሩ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች

3. በጡረታና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ የተገለላችሁ የጤና ባለሙዎች (ለመደበኛ አገልግሎት)

4. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን

5. የጤና ተማሪዎች (በመንግስትና በግል)

በመሆኑም መመዝገብ የሚፈልጉ ሰዎች በጤና ሚኒስቴር ድረገፅ (http://www.moh.gov.et/ejcc/am/node/201)እንዲመዘገቡ ሀገራዊ ቀርቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.