Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 39 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መለሰ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 39 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ።

ኤምባሲው በጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር ነው በሳምንቱ ውስጥ ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ  ያደረገው፡፡

ከፍልሰተኞች መካከል 10 ያህሉ በየመን በአስከፊ ችግር ውስጥ ቆይተው ወደ ጅቡቲ የገቡ ሲሆኑ÷ ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሻገር ጅቡቲ ከገቡ በኋላ ባህር የመሻገር ሀሳባቸውን ለመቀየር የተገደዱ ናቸው ተብሏል፡፡

ከተመላሽ ፍልሰተኞች መካከል 20 ያህሉ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን በጂቡቲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.