Fana: At a Speed of Life!

ለድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል 22 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና መሳሪያ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚኒሶታ ድሬ ኬር ማህበር ለድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታልና በስሩ ለሚገኘው ፈረንሳይ ሆስፒታል 22 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ በአሜሪካ ሚኒሶታ የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች በጋራ ያደረጉት መሆኑ በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እንደገለጹት÷ በሌሎች የውጭ ሀገራት የሚገኙ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆች መሰል ድጋፎችን በማድረግ ለወገኖቻቸውና ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የድሬደዋ አስተደደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በበኩላቸው÷ መሰል ድጋፎች ለከተማዋ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የተሻለ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ድጋፉን ያበረከተው በሚኒሶታ ድሬ ኬር ማህበር ተወካይ አቶ ፊላ አህመድ ማህበራቸው ከዚህ በፊት የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው÷ በቀጣይም ክፍተት ባለባቸው መስኮችም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአልትራሳውንድ ማሽኖች፣ ዊልቼርና ለፅኑ ህሙማን ተኝቶ መታከሚያ ዘመናዊ አልጋዎችና ሌሎች የህክምና ቁሳቁስ በድጋፉ ተበርክተዋል፡፡

በነስሪ ዩሱፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.