Fana: At a Speed of Life!

ሀንጋሪ የአውሮፓ ፓርላማ እንዲበተን ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የአውሮፓ ፓርላማ እንዲበተን ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ህብረት ምክትል ፕሬዚዳንት በሙስና ምክንያት መታሰራቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ እምነት የሚጣልበት አይደለም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ግሪካዊቷ ፖለቲካኛ እና የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢቫ ካይሊ በዚህ ወር ከኳታር ጉቦ ተቀብለዋል በሚል በሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን ተከትሎ መሆኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን እንዳሉት በቅርቡ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውስጥ የተከሰተው የሙስና ቅሌት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አሁን ባለው መልኩ መቀጠል እንደሌለበት አመላካች ነው ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ቀድሞውንም ጥሩ ስም አልነበረውም ሲሉም አክለዋል፡፡

ሃንጋሪያውያን የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አሁን ባለው መልኩ እንዲቀጥል እንደማይፈልጉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ኦርባን የሙስና ቅሌቱ ተቋሙ የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት ሊበጅለት እንደሚገባ አመላካች ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.