Fana: At a Speed of Life!

ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲሸጥ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገልጸዋል።

መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር የጠቀሱት አቶ ተሻለ በዚህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች፥ ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር ተናግረዋል።

በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው ብለዋል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ነው የተናገሩት።

መንግስት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም መንግስት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

በግብይቱ ውስጥም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እያንዳንዱ ፋብሪካ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም አከፋፋዩን የመምረጥ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበትም ነው የተናገሩት።

በመሳፍንት እያዩ

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.