Fana: At a Speed of Life!

የገዳ ባንክ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገዳ ባንክ ስራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የገዳ ባንክ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ስራውን መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ከ28 ሺህ በላይ በሚደርሱ ባለአክሲዮኖች በተሰባሰበ 552 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታልና 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል ነው ስራ የጀመረው።

ገዳ ባንክ በመጀመሪያ ዙር ከ30 በላይ ቅርንጫፎች እንደሚኖሩት አስታውቋል።

የቁጠባ ባህልን በማሳደግ በተወጠነው የባንኩ ስትራቴጂ በመታገዝ ለገጠሩም ማህበረሰብ ተገቢውን የብድር አገልግሎት በማቅረብ የሚታየውን ክፍተት ወደ ዕድል ለመቀየር በትጋት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.