Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በባለሃብቶች የለሙ የእርሻ ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በባለሃብቶች እየተሰሩ የሚገኙ የእርሻ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
 
በክልል ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው የእርሻ ልማት ስራ ከፍተኛ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ መሆኑ በጉብኝት መርሐ ግብሩ ወቅት ተገልጿል፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድር አወል የክልሉ መንግስት የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ትኩረት በመስጠት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
በተለየ መልኩ ባለሃብቶች የጥጥ እርሻ ልማት ላይ እየሰሩ ከሚገኙት ስራ በተጨማሪ በጎን ለምግብ የሚሆን የሽንኩርት፣ የበርበሬ፣ ቲማቲም እንዲሁም የሃብሃብ ምርቶችን በማምረት ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸው ተገልጿል፡፡
 
ባለሀብቶቹ የሚያጋጥማቸውን የገበያ እጦት በተመለከተ በመንግስት በኩል አስፈላጊ የሆኑ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ አወል አርባ መናገራቸውን የአፋር መገናኛ ብዙሓን ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.