Fana: At a Speed of Life!

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንና ዩኒቨርስቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እና የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ እንዲሁም የመንግስት ዩኒቨርሰቲዎችን በመወከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ተፈራርመዋል።

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ፥ ሥምምነቱ ኮሚሽኑ በክልል ዋና ከተሞች በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ጽህፈት ቤቶችን ለመክፈት ያስችለዋል ነው ያሉት።

በዚህም ኮሚሽኑ በሀገሪቱ በሚገኙ 44 ዩኒቨርሲቲዎችና በሁሉም ግቢዎቻቸው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን እንደሚያቋቁም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው ÷ ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተባብሮ መስራቱ የተቋቋመበትን ተልዕኮ ለመወጣት እንደሚያስችለው ም ነው የተናገሩት።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር፣ ኅብረተሰቡን በማወያየት፣ አዳራሽ በማመቻቸትና ባለሙያዎችን በማቅረብ እንደሚተባበሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.