Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ባለሃብቶቿን በግብርና፣ በማዕድንና በሌሎች መስኮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደምታበረታታ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ባለሃብቶች በግብርና፣ በማዕድን ልማትና በሌሎች መስኮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደሚያበረታቱም በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛኦ ዚያን ገልጸዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሣደር አምባሳደር ዛኦ ዚያን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ስለክልሉ አጠቃላይ ሁኔታ ለአምባሣደር ዛኦ ዚያንና ለልዑካን ቡድናቸው ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያና ቻይና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ ግንኙነታቸውን አጠናክረው የቆዩ ሀገራት መሆናቸውንም ነው የገለጹት።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የተፈጥሮ ሃብቶች እንዲሁም በማዕድናት የበለጸገ መሆኑን ገልጸው ፥ ጥቂት ሠርተው ብዙ የሚያተርፉበት አካባቢ መሆኑንም ተናግረዋል።

የቻይና ባለሃብቶች በቤኒሻንጉል በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡት አቶ አሻድሊ ፥ ለኢንቨስትመንት ወደክልሉ ለሚመጡ ባለሃብቶች መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ዛኦ ዚያን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተገኝተው ላደረጉት ድጋፍ አቶ አሻድሊ ሀሰን ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሣደር ዛኦ ዚያን በበኩላቸው ፥ በክልሉ ተገኝተው ባደረጉት ጉብኝት መደሠታቸውን ጠቁመው ፤ ስለክልሉ ለተደረገላቸው ገለጻም አመስግነዋል።

የቻይና ባለሃብቶች በግብርና፣ በማዕድን ልማትና በሌሎች መስኮች እንቨስት እንዲያደርጉ እንደሚያበረታቱም አምባሳደሩ መግለጻቸውም ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አምባሣደር ዛኦ ዚያን በአሶሳ ዞን ኡራ ወረዳ ሆሃ ቁጥር 10 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው 1 ሺህ ቦርሣ፣ 1 ሺህ በሶላር የሚሠሩ መብራቶችንና ሌሎች የትምህርት ቁሣቁሶችን ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.