Fana: At a Speed of Life!

በመንግስት ምስጢራዊ መረጃ ምደባና ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ሚስጢራዊ መረጃ ምደባና ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ እና የቴክኖሎጂ ዝግጁነት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

አዋጁ የመንግስት መረጃዎችን ለመምደብና በየወቅቱ ለመፈተሽ እንዲቻል እና ሚስጢራዊ መረጃዎች እንዲጠበቁ እንዲሁም እንዳይሰራጩ ለማስቻል የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት የሚያስችል ነው።

በጸጥታ መዋቅርም ሆነ በመንግስት የመረጃ ምስጢራዊነት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን ሚስጢራዊ የመረጃ ምደባ እና ጥበቃ ማድረግ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

መሰል ስርዓትን መተግበሩ ሃገራዊ ምስጢርን በተለይም ወታደራዊ የግዥና ሌሎች የመረጃ ምስጢሮችንም ለመጠበቅ የሚስችል መሆኑም ነው የተገለጸው።

ከመንግስት የመረጃ ምስጢር ምደባ በሚደረገው ውይይት ገንቢ ሃሳቦችን እና ግብአቶች መሰብሰብ ለማስቻል ነው ተብሏል።

አዋጁ ትላልቅ የሃገር መረጃዎችን ምስጢራዊነት ጠብቆ እና ህዝብም ደግሞ ማግኘት ያለበትን የመረጃ ሚዛን ጠብቆ ለማስኬድ የሚያስችል ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ መፍጠርን አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

የፍትህ ስርዓት ያልተበጀላቸውን የመረጃ አጠቃቀሞችንም ለማስተካከል የመረጃ ምደባና ጥበቃ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነም ተነስቷል።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.