Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካን በወላይታ ሶዶ ከተማ መርቀው ከፈቱ፡፡

ፋብሪካው በወላይታ ሶዶ ከተማ የተገነባ ሲሆን፥ ከዳቦ በተጨማሪ 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም አለው ተብሏል።

ፋብሪካውን በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት አማካኝነት፥ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ሂቤይ ፒንግል ማሽነሪስ አጋርነት የተገነባ ነው።

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በ11 ከተሞች ተመሳሳይ አቅም ያላቸው ዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን በጋራ ለመገንባት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ጋር ከተፈራረመ በኋላ ፅህፈት ቤቱ ሁለተኛውን ዳቦ ፋብሪካ ነው ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ ያስመረቀው።

በአላዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.