Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረቅ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ ሽልማት በአራት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረቅ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ ሽልማት በአራት ዘርፎች ዕጩ ሆነ ቀረበ።

አየር መንገዱ በሚሰጠው የደረቅ ጭነት ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ነው በስታት ታይምስ የደረቅ ጭነት አገልግሎት ሽልማት ዕጩ ሆኖ የቀረበው።

የሽልማት ሥነ ስርዓቱ የፊታችን የካቲት አጋማሽ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ እንደሚካሔድ የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።

በዓመቱ ፈጣን፣ የተረጋጋና ደኅንነቱ የተጠበቀ የጭነት አገልግሎት የሰጠ አየር መንገድ በስታት ታይምስ በኩል ለሽልማት እንደሚበቃ ተገልጿል፡፡

በዚህም የዓመቱ ምርጥ የጭነት አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ እና አውሮፕላን ማረፊያ በሚል አሸናፊው አየር መንገድ የሽልማቱ አሸናፊ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.