Fana: At a Speed of Life!

ተመራጩ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራጩ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዳ ሲልቫ በአጠቃላይ 21 ሚኒስትሮችን የሾሙ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ስድስቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት በቀጣዩ ሳምንትም ተጨማሪ ሚኒስትሮችን እንደሚሾሙ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ከቀደሙት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የካቢኔ ቁጥር ላቅ ያለ እንደሚሆንም ነው የተነገረው።

ትልቅ ካቢኔ ተጨማሪ ወጪ ማለት አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ሚኒስትሮች ቀበቷቸውን ጠበቅ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በአዲሱ ካቢኔያቸው የፓርቲያቸውን ሁለት አባላት የትምህርት እና ደህንነት ስርዓት እንዲመሩ መምረጣቸውን የቲ አር ቲ ዘገባ ያመላክታል።

ሉላ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት በታኅሣሥ 2022 ይህንን መንግስት ስንቀበል ያገኘናት ብራዚል ጥሩ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ያለች መሆኗን የብራዚል ህዝብ እንዲያውቅ እንፈልጋለን ብለዋል።

እኛ የምንፈልገው ብቃት ያላቸውን እና በጋራ ጥሩ መንግስት የሚያቀናጁ ውጤታማ ፖለቲከኞችን ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.