Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ለጤና መድኅን አገልግሎት ትግበራ ስኬታማነት የሚደረገው ድጋፍ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የጤና መድኅን አገልግሎት ትግበራ ስኬታማነት የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የማሕበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የአፈፃፀም ግምገማና የ2015 ክልላዊ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የጤና መድኅን አገልግሎት በክልሉ ተግባራዊ መደረጉ የክልሉ ሕዝብ ካለበት የኢኮኖሚ ደረጃ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡

ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በጎግ፣ በላሬ እና ጎደሬ ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ መቆየቱን እንዲሁም በአቦቦ፣ ጋምቤላ፣ መንገሺ እና ማኩዌይ ወረዳዎች ደግሞ የጤና መድኅን አገልግሎት እንደሚጀመር አብራርተዋል፡፡

የኢትዮዽያ የጤና መድኅን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ፍሬሕይወት አበበ ÷ እንደ ጋምቤላ ክልል አገልግሎቱን ሲሰጡ የነበሩ ወረዳዎች የተሻለ አፈፃፀም አሳይተዋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አሁን የተካተቱት አራት ወረዳዎችም ከነባሮቹ ልምድ በመውሰድ አባላትን የማብዛት ሥራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.