Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሙስና እና ብልሹ አሠራር ፈፃሚዎችን ለማጋለጥ የጥቆማ መስጫ መስመር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሙስና እና ብልሹ አሠራር ፈፃሚዎችን ለማጋለጥ የጥቆማ መስጫ ነፃ የስልክ መስመር (9080) መዘጋጀቱን የክልሉ የፀረ-ሙስና ኮሚቴ ገለጸ።

የክልሉ የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ እና የፀረ-መስና ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰይድ ባበክር እና የኮሚቴው አባል እና የክልሉ ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር መንግሥት ላሎ የኮሚቴውን ዝግጅት እና ቀጣይ ሥራዎች በተመለከተ ለጋዜጠኞች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ሰይድ ባበክር የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚቴ በመንግሥት እና በሕዝብ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚሠራ ጠቁመው፥ ለዚህም አስፈላጊውን ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደሥራ ገብቷል ብለዋል።

ኅብረተሰቡ ከዛሬ ጅምሮ በ9080 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት እንደሚችልም ነው የተናገሩት።

ከዚህ በተጨማሪ በጽሑፍ እና በአካል በመቅረብ የሙስና እና ብልሹ አሠራር ጥቆማ መስጠት የሚችልበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል።

ከኅብረተሰቡ የሚሰጡ ጥቆማዎችን የሚቀበል የምርመራ እና የትንተና ባለሙያዎችን ያካተተ ቡድን የተደራጀ ሲሆን ዛሬ ሥራ እንደሚጀምር መናገራቸውን የክለሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.