Fana: At a Speed of Life!

በአርሶ አደርና አርሶ አደር ልጅ ስም ለ22 ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ የተሰጠ ካርታ እንዲፀና አድርገዋል በተባሉ ተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጅ ስም ለ22 ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ የተሰጠ ካርታ እንዲፀና እና መብት እንዲፈጠርላቸው አድርገዋል በተባሉ 43 ተከሳሾ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ፡፡
ከባድ የሙስና ወንጀል ከተመሰረተባቸው መከካከል የለሚኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ግርማን ጨምሮ በየደረጃው በክፍለ ከተማው እና በወረዳዎቹ በአመራርና በባለሙያነት ሲያገለግሉ የቆዩ 43 ተከሳሾ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተከሳሾቹ 8 ሺህ 35 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የመንግስት ይዞታን ለ22 ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ በመስጠት ካርታ እንዲፀና እና መብት እንዲፈጠርላቸው በማድረግ በመንግስት ላይ 8 ሚሊየን 69 ሺህ 101 ብር ጉዳት ያደረሱ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ችሎትም ክሱን ለተከሳሾች በችሎት በማንበብ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡና ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ እንዲያቀርባቸው ለጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.