Fana: At a Speed of Life!

ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የመጨረሻ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲበር ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ኢ ቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የመጨረሻ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ተደረገ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ በኋላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የምርመራ ቡድን በማቋቋም የተለያዩ ጥናቶችን ሲያከናውን ቆይቷል።
የመጨረሻ ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ጫና ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል።
አውሮፕላንኑ ከመብረሩ በፊት አብራሪዎች የታደሰ ፈቃድ መያዛቸው፣ የአውሮፕላኑ የታደሰ የበረራ ፈቃድ መኖሩ፣ ሚዛኑና ክብደቱ በሚገባው ልክ መሆኑ መረጋገጡንም ነው የገለጹት።
የአውሮፕላኑ ኤምካስ የተባለው ክፍል ከሲስተም ውጭ በመሆኑ ሊከሰከሰ እንደቻለም ነው በሪፖርቱ የተመላከተው፡፡
የምርመራ ቡድኑ ከፈረንሳይ እና ከአሜሪካ የተለያዩ ድርጅቶች የተውጣጣ መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ ዳግማዊት ላደረጉት የምርመራ ድጋፍ ማመስገናቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
157 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ እያለ ከሥድስት ደቂቃ በኋላ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ተከስክሶ በወቅቱ የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ የ35 አገራት ዜጎች የሆኑ 157 መንገደኞች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.