Fana: At a Speed of Life!

941 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 941 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ዜጎችም ሁሉም ወንዶች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 17 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.