Fana: At a Speed of Life!

ለዴሞክራሲ እንቅፋት የሆኑ ብልሹ አሰራሮችን መታገል ያስፈልጋል- ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 15 2015 (ኤፍ ) ለዴሞክራሲ እንቅፋት የሆኑ ብልሹ አሰራሮችን በአንድ ላይ መታገል እንደሚያስፈልግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በፀረ ሙስና ትግሉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስልጠና ላይ በአዳማ ከተማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥ ብልሹ አሰራሮች የተፈለገውን የሀገር ግንባታ እንዳይሳካ እያደረኑ ነው ብለዋል።

እነዚህን ብልሹ አሰራሮች በተለይም የሚዲያ ተቋማት ሊታገሉት እንደሚገባ ጠቅሰው፥ ለዚህ ደግሞ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የአቅም ክፍተት፣ የፖለቲካ ሁኔታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተልዕኳቸውን እንዳይወጡ ሲያደርጉ እንደነበርና እነዚህን የአቅም ክፍተቶች ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህ ስልጠናም ያሉትን አቅሞች ለማየትና ለመጠቀም ይረዳል ያሉት ሚኒስትሩ፥ በጋራ ተገናኝቶ በመነጋገርና በመወያየት አቅምን በማጎልበት እንቅፋቶችን ለማስወገድ በጋራ እንቁም ሲሉም መልዕክት አሳልፈዋል።

ስልጠናውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስልጠና ማዕከል፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትና የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን እነንዳዘጋጁት ተገልጿል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስልጠና የተለያዩ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች፣ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

በበታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.