ሩሲያ ኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችል የህክምና መሳሪያዎችን ለአሜሪካ ላከች
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አሜሪካ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንዲስችላት የህክምና መሳሪያዎችን የያዘ አውሮፕላን ለሀገሪቱ ላከች።
ሩሲያ የኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችለውን የህክምና መሳሪያ ለአሜሪካ የላከችው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።
A Russian military transport plane took off from Moscow early on Wednesday headed for the U.S. with medical equipment and masks aboard, Russian state TV reported https://t.co/HMTrwMBx0R pic.twitter.com/yCuDSYThuT
— Reuters (@Reuters) April 1, 2020
በአሜሪካ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ድጋፉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአሜሪካ የሚሞቱትን ሰዎች ለመቀነስ እንዲቻል ነው ብሏል።
ኤኤች124 ግዙፍ እቃ ጫኝ አወሮፕላን የፊት ጭንብልን ጨምሮ ሌሎች መሳሪያዎችን በመያዝ ወደ አሜሪካ ጉዞ መጀመሩን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአሜሪካ በኮሮና ቫይርስ የሞቱት ሰዎች ከቻይና በመብለጥ ከ4 ሺህ በላይ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።
ምንጭ፡- ፎክስኒውስ